አስደሳች ዜና ከወደ ሲያትል
Al-Imran (103) … وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا
“And hold fast, all of you together, to the rope of Allah (i.e. Qur’an), and be

not divided among yourselves…’’

በሀገራችን በተለይ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ይደርስ በነበረዉ ዘመን ተሻጋሪ አስከፊ ችግሮች ሳቢያ የነበሩ ብሶቶችን አግባብ
ባለዉ መልኩ ለመንግስት በማቅረብ ዘላቂ ምላሽ እንዲያገኙ በሚል የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በማዋቀር ድምጻችን ይሰማ
በሚል መርህ ቃል ታጅቦ በሰላማዊ መንገድ የእምነት ነጻነቱን ለማስከበር እንቅስቃሴ ሲጀመር በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ
ኮምዩኒቲዎች እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ተንቀሳቅሰዋል ።
በዚያ ወሳኝ ሂደት የጉዳዩ ግዙፍነት፤ አጣዳፊነት እና ወቅታዊነት የተነሳ ይደረጉ የነበሩ ርብርቦሾች የታሰበዉን ለዉጥ በሚፈለገዉ
መልኩ ለማምጣት ባለመቻላቸዉና በመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችን እንዲሁም ከነሱ ጋር ተያዣዥነት ባለዉ መልኩ በግፍ
ለእስር የተዳረጉ በርካታ ሙስሊም ወንድምና እህቶች ላይ በመንግስት አማካይነት እለት ከእለት ይፈጸም የነበረዉ በደል የከፋ
ስለነበር ሂደታችንን ዉስብስብ አድርጎት ነበር።
ያም ሆኖ የታሰቡትን ለዉጦች በሚፈለገዉ መልኩ ለማምጣት ባለመቻላቸዉ በህዝበ ሙስሊሙ ብሎም በኮምዩኒቲዎች
መካከል የአካሄድ ልዩነት መፈጠሩና የነበሩ ሁኔታዎችም ፈር እስከሚይዙ በሚል መስራች ከነበሩ ኮምዩኒቲዎችም ከበድር
ራሳቸዉን ማግለላቸዉ ይታወቃል። ከነዚህም ዉስጥ የበድር ድርጅትን በአባልነት ከመሰረቱ ቀደምት ኮምዩኒቲዎች አንዱ የሆነዉ
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማህበር በሲያትል (ኢማስ ) መሆኑ ግልጽ ነዉ። ሆኖም በተፈጠረዉ የአካሄድ ልዩነት ሳቢያ ከመለያየት
ይልቅ ወደፊት በጋራ የሚጠበቅብንን ተግባራት በብቃት ለመወጣት እንድንችል ከአጋር ድርጅቶች ጋር መዋሀድ ብሎም አንድነታችንን
ማጠናከር ከግዴታዎቻችን አንዱ ነዉ በማለት፤ በወቅቱ የነበሩ ሂደቶችን በመገምገም የኢማስ ኮምዩኒቲ ዳግም በድርጅቱ
ለመቀላቀል ወስነዋል ።
በድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅትም ኢማስን በመቀበል የድርጅቱ አካል ማድረግ በመቻሉ አላህን (ሱ.ወ)
እያመሰገን ይህን የተቀደሰ መልካም ሀሳብ ከግምት ዉስጥ በማስገባት ሌሎች ኮምዩኒቲዎችም እንዲከተሉትና አሉ የምንላቸዉን
ችግሮች በዉይይት በመፍታት ጠንካራ ድርጅት እንዲሆን ማብቃት የሁላችንም ሀላፊነት ብሎም ጥረት ይጠይቃልና በዚሁ አጋጣሚ
የዘወርት ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን ።
አላህ (ሱ.ወ) አንድ ያድርገን አሜን !
በድር ኢትዮጵያ ሰሜን አሜሪካ November 28,2018

Leave a comment

All comments are moderated before being published