Document transfer

Image

Image

አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ፥በነፍሶቻቸው ያለውን (ሁኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም (አር-ራዕድ: 11)  

አዲሱ የበድር ኢትዮጵያ የዳይሬክተሮች ቦርድ የስድስት ወር የስራ ሪፖርቱን በFebruary 15, 2015 ሲያቀርብ የድርጅቱ  የስአፈፃፀምና የገንዘብ አያያዝ ሰነዶች ርክክብ በጊዜው በእንጥልጥል ላይ እንደነበር እንዲሁም የርክክቡን ሂደት በቀጣይነት እንደሚያሳውቅ መግለፃችን ይታወሳል።   

በዚሁም መሰረት የድርጅቱ የዳይሬክተሮችና የትረስቲ ቦርድ  ተወካዮች በApril  ወርመጨረሻ Washington, D.C. በአካል በመገኘት የድርጅቱ የቀድሞ አመራሮች ያቀረቧቸውን ሰነዶችና ንብረቶች በአላህ (.) ፍቃድ ተረክበዋል። በርክክቡ ወቅትም ለጊዜው ያልተገኙ ሰነዶችን በተመለከት የቀድሞ አመራር አባላት የሰነዶቹን ኮፒዎች ከሰነዶቹ ምንጮች በቀጥታ እንዲጠይቁ ተደርጎአል።    

አዲሱ የበድር ኢትዮጵያ የዳይሬክተሮች ቦርድና የስራ አመራር እነዚህ ንሰነዶች ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች በጥልቀትና በጥንቃቄ የመመርመር ሥራ በቀጣይነት የሚያካሂዱ ሲሆን የምርመራውንው ጤትም ለአባል ድርጅቶች በዝርዝር ያሳውቃሉ። በተጨማሪ በምርመራ ውወቅት የሚታዩ ጤናማ አሰራሮችን የበለጠ በማጠናከር ደካማ አሰራሮችን ደግሞ በማሻሻል በአላህ (.) እርዳታ የድርጅቱ የወደፊት የሰነድና የሂሳብ አያያዝ ስርዓት ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖረው ከማድረግ በተጨማሪ ከበድር ኢትዮጵያ ጋር የሚነፃፀሩ ሌሎች ባደጉት አገሮች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ከትርፍ ነፃና ለረጅም አመታት የቆዩ ድርጅቶች እንደሚያደርጉት አመታዊ ኦዲት የተደረጉ የሂሳብ ሪፖርቶችን ለአባላትና ሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች በጊዜ የማቅረብ ሥራ እንዲ ጀመር አስፈላጊው ጥረት ሁሉ ይደረጋል።         

         አላህ (ሱወ) ዑማችንን ለማገልገል ለምናደርገው ጥረት ሁሉ ችሎታና ትዕግስት እንዲስጠን ሁሌም እንለምነዋለን።    

                                                         በድር ኢትዮጵያ አለም-አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት የዳይሬክተሮች ቦርድ 

                                                                                        ሰሜን አሜሪካ   

                                                                                                              June 28, 2015  

Ramadan-2015/1436

 

logo 

Calligraphic rendition of the Basmala

   ረመዳን ሙባረክ

በድር ኢትዮጵያ በቅድሚያ እንኻን ለ1436 ሂጅራ የረመዳን ወር በስላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን በመላው አለም ዙሪያ ለሚገኙትና እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረስብ በሙሉ ወሩ የስላም፤የፍጥ፤ የነጻነት፤የእኩልነት እንዲሁም የፈጣሪያችን (ሱወ) ምህረትና ርህራሄ ቅርብ እንዲሆንልን በከፍተኛ ደረጃ እንመኛለን።

ይሁንና ሙስሊሙ የፈጣሪዉን (ሱወ) ምህረት ለማግኘት እንዲሁ እጁን አጣጥፎ በመቀመጥ የሚመጣ የምህረትም ይሁን የስራ ዉጤትን ድል ለማግኘት አይሞከርም። እንደ ሀገራችንም የቆየ አባባል:- “ቂም ይዞ ጸሎት ሳል ይዞ ስርቆት” የማይሞከር መሆኑን እንደምንገነዘበዉ ሁሉ፤ እኛም ሙስሊሞች ዛሬ በዚህ በተቀደስው የረመዳን ወር ከፈጣሪያችን የምንማጸነው ነገር አንዱ ምህረትን በመሆኑ ያለንን መጠነኛ ልዩነቶች አጥብበን ወደ አንድነት በሚያቃርብ መልኩ ተደጋግፈን የፈጣሪያችንን ምህረት እየጠየቅን፤ ራሳችንንም በእዉነቱ ጎዳና ብቻ አሰልፈን በፈጣሪያችን እርዳታ ወደ ምህረቱና ወደ ድሉ ደጃፍ እንዲያቃርበን አጥብቀን እንለምነዋለን።

ሙስሊሙ ማህበረስብ በኢትዮጵያም ይሁን በመላዉ አለም፡ ብቸኛዉን ጌታዬን ብቻ ነዉ የምገዛውና መሪዎቼንና የሚያስተዳድሩኝ ለመምረጥ እድል ይሰጠኝ ብሎ ስለ ጠየቀ ብቻ ያለምንም ወንጀል በየእስር ቤቶች መማቀቅ ከጀመረ እንሆ እንደቀልድ ወራቶችን ሳይሆን አመታቶችን በማስቆጠር ላይ ይገኛል።

በመሆኑም ይህ የረመዳን ወር በዉጪ በነጻነት እንደልቡ ተነቀሳቅሶ ከበተሰቦቹና ከሙስሊም ወንድምና እህቶች ጋር በስላም እየጾመና እያፈጠረ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ (ኡማ) ነጻነትና እኩልነት ሲሉ በየእስር ቤቱ ቤተስቦቻቸዉንና ልጆቻቸዉን ትተው እነሆ ለአመታት በእስር በመማቀቅ ላይ ለሚገኙ ወንድምና እህቶች በዚህ የአላህ ጥሪ ቅርብ በሆነዉ ወር የእስረኞች ግፍ አብቅቶ ከቤተሰቦቻቸውና ከወከላቸው ማህበረሰብ የሚቀላቀሉበት ጊዜ ቅርብ እንዲሆን ሁላችንም ፈጣሪያችን አላህን በጋራና በአንድነት እንድንለምነዉና እኛም ከፈጣሪያችን ምህረትን እንድንጠይቅ በድር ኢትዮጵያ በዚህ አጋጣሚ መልክቱን ለኢትዮጵያ ሙስሊም በሙሉ መልዕክቱን ማስተላለፍ ይወዳል።

ከዚህም በተጨማሪ ይህ ወር የኢባዳና የሰደቃ ወርም በመሆኑ፤ በረመዳን ወርም ለታሳሪ ወንድምና እህቶቻችን አንዲሁም ቤተሰቦችና ልጆቻቸዉ፤ እኛም ከአላህ ምህረትና ራህመቱን እንደምንጠብቀዉ ሁሉ፤ ለሌሎች እጃችንን እንድንዘረጋ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

በመጨረሻም ፈጣሪያችንን አላህ ይህንን የረመዳን ወር በሰላም ጀምረን በሰላም እንድንጨርስና ስራችንና ጸሎታችን (ዱኣችን) እንዲሁም መልካም ስራችን ነገ ከሱ ፊት ቀርበን የምዳበት እንዲያደርግልን እለምዋለን።

                                        መልካም ረመዳን

በድር ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ድርጅት

ሰሜን አሜሪካ -ጁላይ 17, 2015

Ramadan-1436

 

For More Reading

English
Amharic

Badr Affiliates

 • Icon 04
 • Icon 02
 • Icon 05

About Us

WHAT WE DO

 • Da'awa
 • Unity
 • Advocancy
 • Development

Departments

 • Da'awa
 • Media
 • Finance
 • Convention
 • Community Relations
 • Badr Sisters
 • Youth
 • Ethiopian Relations
 • International Relations
 • Marriage