Press Release in PDF version

የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የተላለፈውን ኢፍትሃዊ የፍርድ ውሳኔ በሚመለከት ከበድር ኢትዮጵያ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

وَيَمْكُرُونَ وَيَمْكُرُ اللَّهُ ۖ وَاللَّهُ خَيْرُ الْمَاكِرِينَ

 “…ይመክራሉም አላህም ተንኮላችውን ይመልስባቸዋል፤ አላህም ከመካሪዎች ሁሉ በላይ ነው።” አል-አንፋል (8:30)

የተራዘመ የፍርድ ሂደት የፍርድ ጉደለት ነው እንደሚባለው ሁሉ፤ ለሦስት ዓመት ሲጓተት የቆየው የኮሚቴዎቻችን የፍርድ ጉዞ ይኸውና እንዲህ  አሳዛኝና አስደንጋጭ አንዲሁም መላ ሙስሊሙን በሚያስቆጣ መልኩ የፍርድ ጉድለትንና የሙስሊሙን ሕገመንግስታዊ የመብት ጥያቄ ባላገናዘበ መልኩ ተወስኗል። ይህ ውሳኔ የሙስሊሙን ማሕበረሰብ ሰላማዊና ሕጋዊ ትግል በኣሸባሪነት ቀለም ቀልሞ የህዝቡን ሰነልቦናዊ ግንዛቤና የህሊና ንቃት ለማሽመሽመድና እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ዳግም መብቱን እንዳይጠይቅ ታቅዶ የተበየነ የፖሊቲካ ድራማ ሲሆን፤ ሙስሊሙ ማሕበረሰብ ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ  አንድነቱን አጠናክሮና ሰላማዊነቱን  ጠብቆ  ትግሉን  በማጠናከር  ያነሳቸውን  የመብት ጥያቄ ሙሉ በሙሉ እስኪመለሱለት እና ወክሎ የላካቸው መሪዎቹ እስኪፈቱ ድረስ ያለመታከት ይታገላል።

በድር ኢትዮጵያ የሙስሊሙ ጥያቄ በሰላማዊና በመነጋገር እንዲፈታ ከመንግስትም ሆነ ኮሚቴው ጋር መገናኘቱ ይታወቃል። መንግስት ከሙስሊሙ ጋር ያለውን ቅራኔ አለዝቦ መፍትሄ በመሻት መላ ሙስሊሙን ለእድገትና ብልጽግና በጥሩ መንፈስ እንዲያሰልፈው ሊያግባቡ የሚችሉና መተማመንና መግባባት የሚፈጥሩ እርምጃዎች እንዲወሰድ ጠይቀን ነበር። አሁንም ቢሆን ሕዝበ ሙስሊሙ በመንግስትና በፍትህ ስርአቱ ላይ ሙሉ በሙሉ  ተስፍ እንዲቆርጥ  ካልተፈለገና የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ፤ እንዲሁም በሃገሪቱ እድገትና ብልጽግና መርሃ ግብር ላይ በሙሉ ፍላጎት ተሳታፊ እንዲሆን ከተፈለገ ፤ ከፍርዱ ባሽገር የሚወዳቸውን መሪዎቹን በማንኛውም መልኩ በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱና ከሚወዳቸው ማሕበረሰብና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊና ሕጋዊ ለመብትና ለእምነት ነጻነት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁሌም በአላህ (ሱ.ወ) ፍቃድ ህያው ሁኖ ይኖራል። የመሪዎቹ በነጻና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር መለቀቅ ለአገር ሰላምና መረጋጋት፤ ለእድገትና ብልጽግና ይበጃል ብለንም እናምናለን። በዱዓ፤ በሃሳብና፤ በስሜት፤ ከኮሚቴዎቻችንና ከቤተሰቦቻቸው ጋር አብረን የምንቆም መሆናችንን በድር ኢትዮጵያ አሁንም ያረጋግጣል።

አላህ (ሱወ) በጽናትና በጥበብ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ አጋር እንድንሆን ችሎታና ትዕግስት እንዲስጥን እንለምነዋለን።

በድር ኢትዮጵያ አለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት
የዳይሬክተሮች ቦርድ
ሰሜን አሜሪካ 
August 2015

Page 11 of 14

www.eaman.org/badr-home

Click here or the above picture for more...

 

(በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ)

የአላህ ሰላምና እዝነት በነቢዩ  ሙሀመድ (ሰወ) እና በቤተሰቦቻቸዉ እንዲሁም  የእሳቸዉን  ፈለግ በተከተሉት ላይ ይሁን ።

"There is no good in many of their conferences except the conferences of such as enjoin charity, or goodness, or the making of peace among men. And who so does that, seeking the pleasure of Allah, We shall soon bestow on him a great reward." (Surah Nisaa: 114)

16ኛዉ የበድር ጉባኤ  በናሽቭል

በድር ኢትዮጵያ ከተቋቋመ እነሆ አስራ ስድስተኛዉን አመት አስቆጥሯል፤ በእነዚህ አመታት ዉስጥ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናዉን መቆየቱ ይታወቃል፤ ከሚያከናዉናቸዉም ዋና ዋና ተግባራት መካከል አንደኛዉ በየአመቱ በሚካሄደዉ በበድር ኢትዮጵያ አመታዊ ጉባኤ ሙስሊሙን ማህበረሰብ በማገናኘት የዳዋ  ፕሮግራሞችን ከመተግበሩ አልፎ በተለያዩ አበይት ርእሶችና በወቅታዊ ችግሮች ላይ በመወያየት የመፍትሄ ሀሳቦች መሻትን ያካትታል።

በዘንድሮም ዓመት አስራስድስተኛዉን የበድር ኢትዮጵያ አለም አቀፍ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዘጋጅነት  በተመረጠዉ በናሽቭል ተኒሲ እንደሚካሄድ ስናበስር ከታላቅ ደስታ ጋር ነዉ!!

በዚህ ታላቅ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ከሰሜን አሜሪካ ግዛቶች እንዲሁም ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎችን ጨምሮ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች አንድነታቸዉን ለመግለጽና እስላማዊ ወንድማማችነታቸዉን ለማጠናከር ብሎም በወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ለመመካከር ወደዚሁ ይተማሉ። ከ (ሀምሌ) JULY 28 እስከ 31 /2016 በሚካሄደዉ በዚሁ ታላቅ ጉባኤ ተካፈይ ይሆኑ ዘንድ በድር ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት በታላቅ አክብሮት ጥሪውን ያቀርባል።

አላሁ አክበር !!!

 

በድር ኢትዮጵያ አለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት

የዳይሬክተሮች ቦርድ

ሰሜን አሜሪካ

DECEMBER  2015

Go to top